ኢ/ር ታከለ ኡማ በቤኔሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ የማዕድን ማውጫ ቦታዎችን ከክልሉ ርዕሰመስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጋር በመሆን ተመልክተዋል።
አሻሽሬ አካባቢ ወርቅ በማውጣት ሂደት ላይ የሚገኘውን “አስኮም ማይኒንግ” ከተመለከቷቸው ቦታዎች አንዱ ነው።
ካምፓኒው በአካባቢው ወርቅ እና የከበሩ ማዕድናትን በማፈላለግ ሂደት ላይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ወደ ምርት ለመግባት የሚያስችለውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ሚንስትሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው ተቋሙ በፍጥነት ወደ ምርት መግባትና ሃገሪቷ ከዚህ ሃብት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሂደቱም የአካባቢው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ዋነኛ ትኩረት መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
ከጉብኝቱ በተጨማሪም ኢ/ር ታከለ በክልሉ ከሚገኙ የማዕድን አልሚዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
አልሚዎቹ ከማአድን ልማት ጋር በተያያዘ የመሰረተ ልማት ችግርና የፀጥታ ጉዳዮች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዳይገቡ እንቅፋት እንደሆነባቸው ተናግረዋል።
በክልል ብዙ ሀብት መሆን ያለባቸው ፀጋዎች እንዳሉ የተናገሩት ኢ/ር ታከለ እነዚህ ሀብቶች በተገቢው መንገድ ስራ ላይ እንዲውሉና ችግሮች እንዲፈቱ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከክልሉ ጋር በመሆን እንደሚሰራ ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዘርፋ በዘመናዊ መልኩ እንዲያድግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ኢ/ር ታከለ።