የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ለክልል የማዕድን ፈቃድ ባለሙያዎች የካዳስተር አጠቃቀም ስልጠና ሰጠ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማዕድን ፈቃድን ለማስተዳደር ካዳስተር በመጠቀም ለባለፈቃዶች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

አገልግሎቱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተጨማሪ በሁሉም ክልሎች ወጥ የሆነ የፈቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር እንዲኖር ለማስቻል ከክልል ለተውጣጡ የዘርፉ ባሙያዎች ለአንድ ሳምንት ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ካዳስተር ፈቃድ የተሰጠባቸው እና ያልተሠጠባቸውን ቦታዎች በቀላሉ መለየት ያስችላል፡፡ ባለፈቃዶችም ባሉበት ሆነው አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚያስችል በመሆኑ ጊዜና ጉልበት ይቆጥባል፡፡