የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የዘርፍ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድና የ6ወር ዕቅድ አፈጻጸም ውይይት እየተካሄደ ነው

በማዕድንና ነዳጅ ዘርፎች የማዕድን የምርት አቅርቦት በማሳደግ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እና የ2013 ዓ.ም የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት የተደረገው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ውሃ መስኖና ኢነርጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ነው ፡፡
የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ሚንስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘርፉ በቴክኖሎጂና በሰው ኃይል ማሳደግ ላይ አተኩሮ እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን በዘርፉ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማሳደግም ህጎችን ከማሻሻል ጀምሮ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡
በዘርፉ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬና የሐገር ውስጥ ገቢ ማሳደግ፣የዘርፉን የስራ ዕድል ፈጠራ ማሳደግ፣የምርት አቅርቦትና የኢንዱስትሪ ትስስርን፣ኢንቨስትመንትን በማጎልበት የማዕናትን ክምችት ምጣኔ ማሳደግ፣አዳዲስ የኢንቨስትመንት ማስፋፋት፣የስነ ምድር መረጃ ለኢንቨስትመንትና ልማት ማመንጨት፣የዘርፉን ተቋማዊ አቅም ብቃት ማጎልበት እና የማዕድንና ነዳጅ ኢንቨስትመንትንና የአካባቢ ማህበረሰብን ትስስር ማጠናከር የሚሉት ስምንት ዋና ዋና ግቦች ናቸው፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ከዘርፉ ከ340 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱ የሚታወቅ ነው፡፡በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት በርካታ የሪፎርም ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን ይህም መንግስት ከዘርፉ የሚጠብቀውን ውጤት ለማሳካት ያስችላል ተብሏል፡፡

Leave A Comment